Fana: At a Speed of Life!

አርቲስት ታሪኩ ብርሃኑ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ

 
አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 2፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) አርቲስት ታሪኩ ብርሃኑ (ባባ) ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ፡፡
 
አርቲስት ታሪኩ ብርሃኑ (ባባ) ባደረበት ህመም ምክንያት ከዚህ ዓለም በሞት መለየቱን ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ከቤተሰቦቹ አረጋግጧል፡፡
 
አርቲስት ታሪኩ ብርሃኑ በበርካታ ፊልሞች ላይ በመሪ ተዋናይነት እና በተዋናኝነት ተሳትፏል፡፡
 
አርቲስቱ ከተሳተፈባቸው ፊልሞች መካከል ላውንደሪ ቦይ፣ 300 ሺህ፣ ፍቅር እና ፌስቡክ፣ ኢንጂነሮቹ፣ ህይወቴ፣ ወደው አይሰርቁ፣ ከቃል በላይ፣ ህይወት እና ሳቅ፣ ሀገርሽ ሀገሬ፣ እዮሪካ፣ ከባድ ሚዛን፣ ወፌ ቆመች፣ ይመችሽ ያራዳ ልጅ 2፣ በቁም ካፈቀርሽኝ፣ እንደ ቀልድ፣ እርቅ ይሁን፣ ሞኙ ያአራዳ ልጅ 4፣ ወቶ አደር፣ አባት ሀገር እና ወጣት በ97 በምሳሌነት ይጠቀሳሉ፡፡
 
አርቲስት ታሪኩ ብርሃኑ የአንድ ልጅ አባት ነበር።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.