Fana: At a Speed of Life!

የጋራ የሰላምና የልማት ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤቱ የገና በዓልን በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ከሚገኙ ተፈናቃዮች ጋር አከበረ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 16፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኦሮሚያ ፣የቤኒሻንጉል ጉሙዝ እና የጋምቤላ ክልሎች የጋራ የሰላምና የልማት ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤት የገና በዓልን በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በባምባሲ ከተማ ከሚገኙ ተፈናቃዮች ጋር አክብሯል፡፡

በዕለቱ የህዝብ ለህዝብ ኮንፈረንስም ተካሂዷል፡፡
የኦሮሚያ፣ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ እና የጋምቤላ ክልሎች የጋራ የሰላምና የልማት ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ፍሮምሳ ሰለሞን እንዳሉት÷ተፈናቃዮቹ ከሞቀ ጎጆአቸው ወጥተው አሁን በመጠለያ ካምፕ ውስጥ ስለሚገኙ የገናን በዓል ተደስተው እንዲያሳልፉ በማሰብ በዓሉን በጋራ እንዳከበሩ ገልጸዋል፡፡

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ተወካይ አቶ አሻሪፍ ሀጂ ኑር በበኩላቸው÷ ዘመናትን ያስቆጠረው የክልሎቹ የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት በማህበራዊ፣ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ትስስር የተገነባ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ክልሎቹ በልማትም የተሳሰሩ መሆናቸውን ገልጸው የኦሮሚያ ክልል በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል አሶሳ ዞን የሚያስገነባው አዳሪ ትምህርት ቤትም ለዚህ ማሳያ ነው ብለዋል።

በዘመን በየነ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.