Fana: At a Speed of Life!

የኳስ ንጉሱ ፔሌ በ82 ዓመቱ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ

 

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 20፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ‘’የእግር ኳሱ ንጉስ’’ ተብሎ የሚጠራው ብራዚላዊው ኳስ ተጫዋች ፔሌ በ82 ዓመቱ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ።

ፔሌ በአለም ዋንጫ ታሪክ ሶስት የዓለም ዋንጫዎችን፣ በ1958፣ 1962 እና በ1970 ከሀገሩ ጋር የውድድሩ አሸናፊ በመሆን ብቸኛ ባለታሪክ ነው፡፡

ባለፈው አንድ ወር በአንጀት ካንሰር ሳቢያ ህክምና ሲደረግለት የቆየው ፔሌ ባለፈው ሣምንት አስጊ ሁኔታ ላይ እንደሆነ የተለያዩ ዓለም አቀፍ ሚዲያዎች ሲዘግቡት እንደነበር ይታወሳል፡፡

በዚህም ኳስ ትታዘዝለታለች የሚባልለት የኳስ ጥበበኛው ፔሌ መትረፍ አልቻለም።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.