Fana: At a Speed of Life!

1 ሺህ 70 ኢትዮጵያውያን ከሳዑዲ ዓረቢያ ወደ ሀገራቸው ተመለሱ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 24፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ዛሬ በሶስት ዙር በተከናወነ በሳዑዲ ዓረቢያ በችግር ውስጥ ያሉ ዜጎችን የመመለስ ስራ 1 ሺህ 70 ኢትዮጵያውያንን ወደ ሀገራቸው መመለስ መቻሉ ተገለፀ።
 
በዛሬው እለት ወደ ሀገር ከተመለሱ ዜጎች መካከል 1ሺህ 67 ወንዶች ሲሆኑ÷ ሶስቱ እድሜያቸው ከ18 አመት በታች የሆኑ ታዳጊዎች ናቸው፡፡
 
ለተመላሽ ዜጎች በአውሮፕላን ማረፊያና በማቆያ ማእከላት ተገቢውን ድጋፍ እና እንክብካቤ በማድረግ ከቤተሰብ ጋር የመቀላቀል ስራ እየተሰራ እንደሚገኝ ከሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
 
ከህዳር 12 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ እስካሁን በተከናወነ ዜጎችን ወደ ሀገር የመመለስ ስራ 23 ሺህ 116 ኢትዮጵያውያንን መመለስ ተችሏል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.