Fana: At a Speed of Life!

በጋምቤላ ክልል የተገነባው የአሳ ማቀነባበሪያና የግብይት ማዕከል ተመረቀ

አዲስ አበባ፣ ጥር 1፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በጋምቤላ ክልል ያለውን የዓሳ ሀብት በዘመናዊ መንገድ ለማልማትና ለመጠቀም የሚያስችል የአሳ ማቀነባበሪያና የግብይት ማዕከል ተመረቋል።

ማዕከሉን የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትሩ ዶክተር በለጠ ሞላ እና የጋምቤላ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኡሞድ ኡጁሉ መርቀው ከፍተውታል፡፡

ሚኒስትሩ  ዶክተር በለጠ ሞላ በዚህ ወቅት እንዳሉት÷ ፕሮጀክቱ በግብርና ምርቶች በቴክኖሎጂ በመደገፍና እሴት በመጨመር በአለም ገበያ ተወዳዳሪ የመሆን ዕቅድ አንዱ አካል ነው።

ፕሮጀክቱ ኢትዮጵያ በውጭ ምንዛሬ ከውጭ የምታስገባውን የአሳ ምርት በማስቀረት የውጭ ምንዛሬ እጥረትን ለመቅረፍ እንደሚያስችል ተናግረዋል።

ርዕሰ መስተዳድር  ኡሞድ ኡጁሉ ÷ የአሳ ማቀነባበሪያና የግብይት ማዕከሉ የአሳ ምርትን ለሀገር ውስጥና ለውጭ ገበያ በማቅረብ የሀገሪቱን የአሳ ምርት እጥረትን ይቀርፋል ማለታቸውን ከጋምቤላ ክልል ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

በክልሉ የውሃ ሀብት ከ113 በላይ የሚደርሱ የዓሳ ዝርያዎች እንደሚገኙበት ጠቁመው ከእነዚህ ውስጥ 15ቱ በገበያ ከፍተኛ ተፈላጊነት ያላቸው ዝርያዎች መሆናቸውንም ጠቁመዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.