Fana: At a Speed of Life!

በትግራይ ክልል አምራች ኢንዱስትሪዎችን ዳግም ስራ ለማስጀመር ጥናት እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥር 9፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የሰላም ስምምነቱን ተከትሎ በትግራይ ክልል አምራች ኢንዱስሪዎችን ዳግም ስራ ለማስጀመር ጥናት እያካሄደ መሆኑን የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡
 
በሚኒስቴሩ የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አበባ ታመነ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለጹት÷በትግራይ ክልል በግጭት ምክንያት ስራ ያቆሙ አምራች ኢንዱስትዎችን በፍጥነት ዳግም ስራ ለማስጀመር በቅንጅት እየተሰራ ነው፡፡
 
በዚህ መሰረትም በሚኒስቴሩ የስራ ሃላፊዎች የተመራ ልዑክ ወደ ትግራይ ክልል አቅንቶ ጉዳት በደረሰባቸው አምራች ኢንዱስትሪዎች ላይ የመጀመሪያ ዙር ጥናት እያካሄደ መሆኑን አንስተዋል፡፡
 
ልዑካኑ በእስካሁኑ ቆይታቸውም የመቀሌ ኢንዱስትሪ ፓርክን፣ ሼባ ሌዘር ኢንዱስትሪን፣ሰማያታ እምነ በረድ ፋብሪካን እና ሌሎች ተቋማትን ተዘዋውረው መመልከታቸውን ጠቁመዋል፡፡
 
በጥናቱም ጉዳት የደረሰባቸውን አምራች ተቋማት፣ የጉዳት መጠን፣ አሁን ያሉበትን ሁኔታ እንዲሁም ዳግም ስራ ለማስጀመር የሚያስፍልጉ ግብዓቶችን የመለየት ስራ እንደሚሰራ ጠቁመዋል፡፡
 
በተጨማሪም ልዑካኑ ቡድኑ ኢንዱስትሪዎች ዳግም ስራ በሚጀምሩበት ሁኔታ ላይ ከባለሃብቶች፣ ከፓርክ ሃላፊዎች እና ከባለ ድርሻ አካላት ጋር እየመከረ መሆኑን አስረድተዋል፡፡
 
በመላኩ ገድፍ
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.