በኦሮሚያ ክልል ከአበባ፣ አትክልትና ፍራፍሬ ወጪንግድ ከ301ሚሊየን ዶላር በላይ ገቢ ተገኘ
አዲስ አበባ፣ ጥር 12፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በኦሮሚያ ክልል ባለፉት ስድስት ወራት ከአበባ፣ አትክልትና ፍራፍሬ ወጪንግድ ከ301 ሚሊየን ዶላር በላይ ገቢ መገኘቱን የክልሉ ኢንቨስትመንትና ኢንዱስትሪ ቢሮ ገለጸ፡፡
የቢሮው የኢንቨስትመንት ፕሮሞሽንና ኮሙኑኬሽን ተወካይ ስዩም ሃይሉ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደተናገሩት÷ባለፉት ስድስት ወራት የአበባ የአትክልትና ፍራፍሬ ምርትን ወደ ውጭ በመላክ ከ301 ነጥብ 7 ሚሊየን ዶላር በላይ ገቢ ተገኝቷል፡፡
በክልሉ 2 ሺህ 754 ባለሃብቶች በ95 ቢሊየን ብር ካፒታል ወደ ኢንቨስትመንት ዘርፍ መሰማራታቸውን ተወካዩ አንስተዋል፡፡
ባለሃብቶቹ በግብርና፣ በማኑፋክቸሪንግ፣በአግሮ ኢንዱስትሪና በአገልግሎት ዘርፎች ስራ መጀመራቸውን አመላክተዋል፡፡
በዚህም በዘርፉ ከ77 ሺህ 839 በላይ ለሆኑ ዜጎች የስራ እድል መፈጠሩን ነው የገለጹት፡፡
በፀሃይ ጉሉማ