Fana: At a Speed of Life!

ለበጋ መስኖ ልማት ትኩረት ሰጥተው እየሰሩ መሆኑን የአፋርና ጋምቤላ ክልሎች ገለጹ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 24 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ለበጋ መስኖ ልማት ትኩረት ሰጥተው እየሰሩ መሆኑን የጋምቤላና አፋር ክልሎች ገልጸዋል፡፡

የጋምቤላ ክልል የእርሻና ተፈጥሮ ሃብት ልማት ቢሮ ሃላፊ አጃክ ኡቻን እንዳሉት÷ ክልሉ በበጋ መስኖ የስንዴ ልማት 480 ሄክታር መሬት ለመሸፈን አቅዶ 139 ሄክታር በማልማት ላይ ይገኛል፡፡

ሌሎች ምርቶች የልማቱ አካል መሆናቸውን ጠቁመው ÷ ከስንዴ ምርት በሄክታር 35 ኩንታል ለማግኘት መታቀዱን ተናግረዋል፡፡

በአፋር ክልልም የበጋ መስኖን አካባቢው ተጠቃሚ እንዲሆን 24 ሺህ ሄክታር መሬት ለማልማት በእቅድ መያዙን የክልሉ መስኖና ተፋሰስ ቢሮ ሃላፊ ኢንጅነር ወላ ውጢቃ አንስተዋል፡፡

በክልሉ የነበረውን የጎርፍ አደጋ የመስኖ ፕሮጄክቶችን የሚመግበው መስመር ከፍተኛ ጉዳት አድርሶበት እንደነበር ሃላፊው አስታውሰዋል፡፡

አሁን ላይም በጉዳዩ ላይ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በትኩረት እየተሰራ መሆኑን እና የመስኖ መስመሩ እየተጠናቀቀ እንደሚገኝ ጠቁመዋል፡፡

ሃላፊዎቹ ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ አርሶ አደሩ የበጋ መስኖን በሰፊው እንዲያለማ በርካታ ስራዎች መጀመራቸውን ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ተናግረዋል፡፡

በአሸናፊ ሽብሩ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.