Fana: At a Speed of Life!

የግብር ክፍያዎችን በቴሌ ብር መሰብሰብ የሚያስችል ስምምነት ተፈረመ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 25 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮ ቴሌኮም እና የገቢዎች ሚኒስቴር የግብር ክፍያዎችን በቴሌ ብር ለመሰብሰብ የሚያስችል ስምምነት አደረጉ።
 
ስምምነቱ ግብር ከፋዮች የግብር ክፍያዎችን ቴሌ ብር የዲጂታል ክፍያ ስርዓት ተጠቅመው በየትኛውም ጊዜ እና ቦታ ሆነው እንዲከፍሉ የሚያስችል ነው ተብሏል።
 
ተገልጋዮቹ በኦንላይን አገልግሎት፣ በቴሌብር የሞባይል መተግበሪያ ወይም በአጭር የጽሁፍ መልዕክት *127# በመጠቀም ክፍያቸውን እንዲፈፅሙ የሚያስችል ነው።
 
በማህሌት ተክለብርሀን
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.