Fana: At a Speed of Life!

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ወደ ትግራይ ክልል የሚደረጉ በረራዎች እንዲፋጠኑ መመሪያ ሰጡ- አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን

አዲስ አበባ፣ ጥር 26፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ወደ ትግራይ ክልል የሚደረጉ በረራዎችን ጨምሮ ሌሎች አገልግሎቶች እንዲፋጠኑ መመሪያ መስጠታቸውን የጠቅላይ ሚኒስትሩ የብሔራዊ ደኅንነት አማካሪ ሚኒስትር አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ገለጹ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ወደ ክልሉ የሚደረጉ በረራዎች እንዲጨምሩ፣ የባንክ አገልግሎት እንዲፋጠን እና ሌሎች እርስ በርስ መተማመንን የሚያጎለብቱ እና የዜጎችን አኗኗር የሚያቀሉ አገልግሎቶች እንዲፋጠኑ መመሪያ ማስተላለፋቸውን ነው የብሔራዊ ደኅንነት አማካሪው በትዊተር ገጻቸው ያሰፈሩት።

የፌዴራል መንግሥት እና የህወሓት የሰላም ስምምነት ኮሚቴ አባላት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በተገኙበት ለመጀመሪያ ጊዜ በዛሬው ዕለት በሐላላ ኬላ ተገናኝተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለመጀመሪያ ጊዜ ከሰላም ስምምነት ትግበራ አስተባባሪ ኮሚቴ ጋር ምክክር ያደረጉ ሲሆን፤ በውይይቱ እስካሁን በሰላም ስምምነቱ አፈፃፀም ዙሪያ የተከናወኑ ተግባራት ተገምግመዋል፡፡

በቀጣይም ትኩረት በሚያስፈልጋቸው ጉዳዮች ላይ አቅጣጫ ተቀምጧል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.