Fana: At a Speed of Life!

ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ ባሳዩት አጋርነት የሱዳን ህዝብ ተደስቷል- የሱዳን ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር

አዲስ አበባ ፣ ጥር 27 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ባሳዩት አጋርነት የሱዳን ህዝብ ተደስቷል ሲሉ የሱዳን ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደፋላ ኤልሃጅ አሊ ተናገሩ፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ ከሱዳን ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ደፋላ ኤልሃጅ አሊ  ጋር ተወያይተዋል።

በውይይታቸው አምባሳደር ምስጋኑ ÷በኢትዮጵያና በሱዳን መካከል ያለውን የቆየ የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት አድንቀዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ  በሱዳን ያደረጉት ጉብኝትም ለሱዳን ህዝብና መንግስት ያላቸውን ሁሉን አቀፍ አጋርነት ለማሳየት መሆኑን ገልፀዋል፡፡

የሱዳን መንግስት ከአፍሪካ ህብረት አባልነት መታገዱ ኢትዮጵያን እንደሚያሳስባት የገለፁት አምባሳደሩ  ሱዳንን ወደ ህብረቱ አባልነት ለመመለስ የኢትዮጵያ መንግስት ጥረት እንደሚደርግ አመላክተዋል፡፡

እንዲሁም  በድንበር አካባቢ የሚከናወኑትን ህገ-ወጥ ንግድና የተደራጁ ወንጀሎችን ለመግታት በትብብር ለመስራት የኢትዮጵያ መንግስት ቁርጠኛ መሆኑን አስገንዝበዋል፡፡

አምባሳደር ደፋላ ኤልሃጅ አሊ በበኩላቸው÷ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በካርቱም ያደረጉትን ጉብኝት እና ከሁሉም የሱዳን የፖለቲካ ቡድኖች ጋር ያደረጉትን ውይይትን አድንቀዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የሱዳንን የፖለቲካ ቀውስ በተመለከተ ላሳዩት አጋርነት እና አቋምም የሱዳንን ህዝብ ያሰደሰተ ነው ማለታቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.