Fana: At a Speed of Life!

የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ውጤት ያመጡ ተማሪዎች የተቋም ምርጫቸውን እስከ ፊታችን የካቲት 2 ቀን ድረስ ማስተካከል ይችላሉ-ሚኒስቴሩ

አዲስ አበባ፣ ጥር 29፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ ሀገር አቀፍ ፈተና ወስደው 50 ከመቶ እና ከዚያ በላይ ያመጡ እና በመንግስት ተቋማት ገብተው መማር የሚፈልጉ ተማሪዎች የተቋም ምርጫቸውን በየትምህርት ቤታቸው እስከ የካቲት 02 ቀን 2015 ዓ.ም ድረስ ማስተካከል እንደሚችሉ የትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

በሌላ በኩል ለ2015 የትምህርት ዘመን በልዩ ሁኔታ በአዳማ እና አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲዎች የመግቢያ ፈተና የማይሰጥ መሆኑ ተገልጿል፡፡

ስለሆነም በእነዚህ ዩኒቨርሲቲዎች መማር የሚፈልጉ የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች የመግቢያ ፈተና የማይሰጥ በመሆኑ መርጠው መመደብ እንደሚችሉ ተጠቁሟል፡፡

በምደባ ወቅት አዎንታዊ ድጋፍ የሚሹ (ተመሳሳይ ጾታ ያላቸው መንትያዎች፣ እመጫቶች (በቅርቡ የወለዱ እናቶች) ፣ ነፍሰጡር ተማሪዎች፣ በመንግስት ሆስፒታሎች ህክምና ቦርድ የተረጋገጠ ልዩ ክትትል የሚሻ ህመም ታማሚዎች … ወዘተ) ተማሪዎች ማመልከቻቸውንና ደጋፊ ሰነዶቻቸውን በቀጣዩ ሊንክ https://student.ethernet.edu.et በኩል ብቻ እንዲልኩ ተመላክቷል፡፡

ሚኒስቴሩ ከሊንክ ውጭ ምንም አይነት ማመልከቻ በአካል የማይቀበል መሆኑንም አስታውቋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.