Fana: At a Speed of Life!

ዶ/ር ፍፁም አሰፋና አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ ከኦማን የኢኮኖሚ ሚኒስትር ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 27፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የፕላን እና ልማት ሚኒስትር ፍፁም አሰፋ እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ ከኦማን የኢኮኖሚ ሚኒስትር ሰዒድ አል ሻኪሪ ጋር ተወያይተዋል፡፡

በውይይታቸውም ኢትዮጵያ እና ኦማን በኢኮኖሚው ዘርፍ ያላቸውን ግንኙነት  ማጠናከር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ  መክረዋል፡፡

ውይይቱ ከ5ኛው የተባበሩት መንግሥታት አዳጊ ሀገራት ጉባዔ ጎን ለጎን የተካሄደ መሆኑን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.