Fana: At a Speed of Life!

ሀገር አቀፍ የምግብ ሥርዓት ማጠናከሪያ ፕሮግራም ስራ ተጀመረ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 30 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ሀገር አቀፍ የምግብ ሥርዓት ማጠናከሪያ ፕሮግራም ስራ ማስጀመሪያ መርሐ ግብር ተካሂዷል።

በድሬዳዋ ከተማ በይፋ የተጀመረው የምግብ ስርዓት ማጠናከሪያ ፕሮግራም÷ በፈረንጆቹ እስከ 2029 ድረስ ለቀጣይ ሰባት ዓመታት የሚተገበር እንደሆነ ተገልጿል።

የግብርና ሚኒስትር ግርማ አመንቴ ፕሮግራሙ በተጀመረበት ወቅት እንደተናገሩት÷ ባለፉት ዓመታት በሀገሪቱ የተመዘገቡት አበረታች ውጤቶች ቀጣይነት እንዲኖራቸው የ10 ዓመታት እቅድ ተዘጋጅቶ ወደ ስራ ተገብቷል፡፡

በ10 ዓመቱ የልማት እቅድ ለሀገር በቀል እውቀቶች ልዩ ትኩረት በመስጠቱ በግብርናው መስክ ምርታማነትን በመጨመር በምግብ ሰብል ራስን ለመቻል የሚያስችሉ ስትራቴጂዎች መነደፋቸውን አንስተዋል፡፡

በዓለም ባንክ የምስራቅ አፍሪካ ዳይሬክተር ኡስማን ዲዮን በበኩላቸው÷ በኢትዮጵያ የተጀመሩ የልማት ስራዎች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ ባንኩ አጋርነቱን እንደሚያጠክር ተናግረዋል፡፡

ባለፉት ዓመታት ከሰሃራ በታች ካሉ ሀገራት ኢትዮጵያ ተከታታይነት ያለው እድገት ማስመገቧን ለድጋፉ አይነተኛ አስተዋጽኦ እንዳለው አውስተዋል፡፡

በኢትዮጵያ እየተመዘገበ ያለው እድገት ቀጣይነት እንዲኖረውና ድርቅና ርሃብ በህዝቡ ላይ ተፅዕኖ እንዳያሳድር በምግብ ሰብል ራስን ለመቻል ለሚደረገው ጥረት ድጋፉን እንደሚቀጥልም አረጋግጠዋል፡፡

በኢትዮጵያ የምግብ ስርዓት ማስጀመሪያ መርሐ ግብር ላይ የሁሉም ክልሎች የግብርና ቢሮ ሃላፊዎችና የልማት አጋሮች ተሳትፈዋል፡፡

በተሾመ ኃይሉ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.