Fana: At a Speed of Life!

አሜሪካ ለኢትዮጵያ ከ331 ሚሊየን ዶላር በላይ የሰብአዊ ድጋፍ ይፋ አደረገች

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 6 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ለሥራ ጉብኝ አዲስ አበባ የሚገኙት የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን ለኢትዮጵያ ከ331 ሚሊየን ዶላር በላይ የሰብአዊ ድጋፍ ይፋ አደረጉ፡፡

አንቶኒ ብሊንከን እንዳስታወቁት ድጋፉ በአሜሪካ ውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤቱ እና በአሜሪካ ዓለም አቀፍ ተራድኦ ድርጅት አማካኝነት የሚሸፈን ነው፡፡

ድጋፉም በተለያዩ ምክንያቶች በችግር ለተጋለጡ ወገኖች ለምግብ፣ ለመድሃኒት፣ ለንጹህ የመጠጥ ውሃ የሚውል መሆኑ ተገልጿል።

ይህም በግጭት ለተጎዱ፣ ለተፈናቀሉ፣ በድርቅ ለተጠቁ እና ለምግብ እጥረት ለተጋለጡ ዜጎች ሕይወት አድን ድጋፍ ማድረግ እንደሚያስችልም ነው የተገለጸው።

ከዚህ ውስጥ 12 ሚሊየን ዶላሩ በአሜሪካ ውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት በኩል የሚደረግ ሲሆን፥ 319 ሚሊየን ዶላሩ ደግሞ በአሜሪካ ዓለም አቀፍ ተራድኦ ድርጅት በኩል የሚደረግ ነው ተብሏል፡፡

የአሁኑ ድጋፍ አሜሪካ በቀጣናው በፈረንጆቹ 2023 ያደረገችውን ድጋፍ ወደ 780 ሚሊየን ዶላር እንደሚያሳድገውም ተጠቅሷል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.