Fana: At a Speed of Life!

የኒውክሌር ቴክኖሎጂ ለሰላማዊ ዓላማ እንዲውል የትብብር ስራዎች ተጠናክረው ሊቀጥሉ ይገባል ተባለ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 8 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በአፍሪካ የኒውክሌር ሳይንስና ቴክኖሎጂን በማጠናከር የኒውክሌር ቴክኖሎጂን ለሰላማዊ ዓላማ እንዲውል የትብብርና ድጋፍ ስራዎች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ ተጠየቀ፡፡
 
በኢትዮጵያ አስተናጋጅነት ለመጀመሪያ ጊዜ ሲካሄድ የነበረው የዓለም አቀፍ አቶሚክ ኤጀንሲ የኒውክሌር ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዘርፍ ዓመታዊ ጉባኤ አቅጣጫዎችን በማስቀመጥ ተጠናቋል፡፡
 
የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር በለጠ ሞላ÷ ጉባኤው ተግዳሮቶችን ለመለየት፣ በመፍትሄዎች ላይ ለመወያየት እና አዲስ የትብብር እድሎችን ለመቃኘት ማስቻሉን ተናግረዋል፡፡
 
በአፍሪካ የኒውክሌር ሳይንስና ቴክኖሎጂን በማጠናከር የኒውክሌር ቴክኖሎጂን ለሰላማዊ ዓላማ እንዲውል የትብብርና ድጋፍ ስራዎች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ ጠይቀዋል።
 
በሁሉም ዘርፎች በተለይም በኒውክሌር ተቋማት ጨምሮ የስራ ፈጠራ ባህልን የማስተዋወቅ ስራ ተጠናክሮ ሊሰራ ይገባል ብለዋል፡፡
 
በቀጣይም ውጤታማ ነባር አሰራሮችን በማስቀጠል፣ አዳዲስ ሀሳቦችን በማመንጨት እና ተጨማሪ አካሄዶችን በማከል፣ በጋራ እና በትብብር በመስራት የኤጀንሲውን ዓላማዎች ለማሳካት በጋራ እንሰራለን ነው ያሉት።
 
የዓለም አቀፉ አቶሚክ ኢነርጂ ኤጀንሲ ምክትል ዳይሬክተር ጀነራልና የቴክኒካል ትብብር ኃላፊ ሚስተር ሊዩ ሁዋ በበኩላቸው÷ ጉባኤው ቁልፍ ጉዳዮች ተነስተው በጋራ የተመከረበትና የጋራ ስምምነት የተደረሰበት ነው ብለዋል፡፡
 
በቀጣይ ለትግበራው በጋራ ለመስራት በዲፕሎማሲው ዘርፍም ከሚመለከታቸው በዘርፉ የበለጸጉ ሀገራት ለአፍሪካ ተገቢውን እገዛ እኔዲሰጡ የበኩላቸውን እንደሚወጡ መግለጻቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.