Fana: At a Speed of Life!

የአካባቢ ጉዳይ ተመራማሪ ዶክተር ተወልደ ብርሃን ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 12፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአካባቢ ጉዳይ ተመራማሪ ዶክተር ተወልደ ብርሃን ገብረ እግዚአብሔር በ83 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ፡፡

ዶክተር ተወልደ ብርሃን ገብረ እግዚአብሔር በአካባቢ ጉዳይ ላይ ለዓለም የሚጠቅም ተጠቃሽ ሥራዎችን ሰርተዋል።

በተለይም÷ በብዝሐ ሕይወት፣ በማሕበረሰብ (የአርሶ አደሮችን መብት) ማስከበር እና በዘረመል ምሕንድስና በሚመረት እህል ላይ ያደረጓቸው ምርምሮች በዓለም አቀፍ ደረጃ ዕውቅናና ሽልማት አስገኝቶላቸዋል ብለዋል፡፡

ከሽልማታቸው መካከል “የአማራጭ የኖቤል ሽልማት” እና “የምድራችን ጀግና” በሚል ሲንጋፖር ላይ በፈረንጆቹ 2006 ላይ የተሸለሙት ይጠቀሳሉ ነው ያሉት፡፡

ሕይወታቸው እስከአለፈበት ድረስም አዲስ አበባ ይኖሩ እንደነበር ነው የቅርብ ወዳጃቸው የሆነው ደራሲ ዘነበ ወላ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት የገለፀው፡፡

ደራሲ ዘነበ ወላም ‹‹የምድራችን ጀግና›› በሚል ርዕስ በጻፈው መጽሐፍ የዶክተር ተወልደ ብርሃን ገ/እግዚአብሔርን የሕይወት ታሪክ እና ሥራዎቹን አስቃኝቷል፡፡

ዶክተር ተወልደ ብርሃን የሦስት ሴቶች ልጆች አባት ነበሩ፡፡

እንዲሁም ከ60 በላይ ሌሎች ልጆችን አሳድገዋል፡፡

ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትም ለሟች ልጆች፣ ዘመድ እና ወዳጆች መጽናናትን ይመኛል፡፡

በዮሐንስ ደርበው

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.