Fana: At a Speed of Life!

ቱርክ በመሬት መንቀጥቀጥ አደጋው 104 ቢሊየን ዶላር የሚገመት ውድመት ደርሶብኛል አለች

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 12፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በዚህ ዓመት በፈረንጆቹ የካቲት 6 ላይ በቱርክ በተከሰተው ከባድ የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ 104 ቢሊየን ዶላር ገደማ ጉዳት መድረሱ ተነገረ፡፡

የቱርኩ ፕሬዚዳንት ሬሲፕ ታይፕ ኤርዶኻን ÷ እንዲህ ያለው አደጋ በራስ ዐቅም ብቻ የሚመከት ባለመሆኑ አጋርነታችሁን የምታሳዩበት ጊዜ አሁን ነው ሲሉ የዓለምአቀፉን ማኅበረሰብ አሳስበዋል፡፡

ኤርዶኻን የድጋፍ ጥያቄውን ያቀረቡት በመሬት መንቀጥቀጥ አደጋው ክፉኛ ለተጎዱት ቱርክ እና ሶሪያ በብራስልስ በተዘጋጀው ዓለም አቀፍ የዕርዳታ ማሰባሰቢያ መድረክ ላይ መሆኑን አር ቲ ዘግቧል፡፡

በሚቀጥለው ዓመት በመልሶ ግንባታ መርሐ-ግብር ከ319 ሺህ በላይ መኖሪያ ቤቶችን ለመገንባት ማቀዳቸውንም ይፋ አድርገዋል፡፡

“በዚህ አስቸጋሪ ጊዜ ከጎናችን ለቆማችሁ አጋሮቻችን ሁሉ ምሥጋናዬ ይድረሳችሁ ፤ ያሳያችሁትን አብሮነት መቼም አንረሳውም” ሲሉም ተናግረዋል።

በመሬት መንቀጥቀጥ አደጋው ከ51ሺህ በላይ ሰዎች ተጎጂ እንደሆኑ እና ከ105 ሺህ በላይ በሚሆኑት ላይ ደግሞ አካላዊ ጉዳት እንደደረሰባቸው ተመልክቷል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.