Fana: At a Speed of Life!

የመደመር ትውልድ’ መጽሐፍን ለዲፕሎማቲክ ማኅበረሰብ አባላት የማስተዋወቅ መርሐ-ግብር ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 14 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) አዲሱን የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ‘የመደመር ትውልድ’ መጽሐፍን ተቀማጭነታቸውን በኢትዮጵያ ላደረጉ የዓለም አቀፍ ዲፕሎማቲክ ማኅበረሰብ አባላት የማስተዋወቅ መርሐ-ግብር ተካሂዷል።

የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በጋራ ባዘጋጁት በዚህ ዝግጅት ላይ የእንግሊዘኛው ቅጂ ለውይይት ቀርቧል።

ከመጽሐፉ ሽያጭ የሚገኘው ገቢ መጪውን ትውልድ በማሰብ በሀገር ውስጥ ለሚሠሩ የልማት ሥራዎች እንደሚውል ተገጠቁሟል።

የዲፕሎማቲክ ማኅበረሰብ አባላት፣ የዓለም አቀፍ ድርጅቶች፣ ዓለም አቀፍ ትምህርት ቤቶችና የንግድ ተቋማት የንባብ ባህልን በማጎልበት ላይ እንዲሳተፉ ጥሪ መቅረቡን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ ቤት መረጃ ያመላክታል፡፡

በመርሐ-ግብሩ የተገኙት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ÷ ‘የመደመር ትውልድ’ እየገጠሙ ያሉ ችግሮችን ለመፍታት የሚያስችሉ አዳዲስ አቅጣጫ ጠቋሚ ሐሳቦች የተካተቱበት መጽሐፍ ነው ብለዋል።

ትውልዶች በጋራ ያለፉበትን፣ የኖሩበትን እና የሚኖሩበትን ሐሳባዊ እውቀቶች በማጣመር ለበለጸገች ሀገር መፈጠር እና እውን መሆን እንዲተጉ የሚያደርግ ሐሳብ እንዳለውም ጠቁመዋል።

የጠቅላይ ሚኒስትሩ ፕሬስ ሰክሬተሪ ቢልለኔ ሥዩም በበኩላቸው÷መጽሐፉ ቀድመው የነበሩ ትውልዶችን ከነገው ትውልድ ጋር የሚያስተሳስር እና በሐሳብ የበላይነት ላይ ተመርኩዞ መነጋገር እና መግባባት ለሀገር ያለውን ጠቀሜታ የሚያጎላ መሆኑን ተናግረዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.