Fana: At a Speed of Life!

በቤላሩስ የሚገኙ ኩባንያዎች በኢንዱስትሪ ፓርኮች የተለያዩ ቁሳቁሶችን ማምረት እንደሚፈልጉ ገለጹ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 15፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ተቀማጭነታቸውን ቤላሩስ ያደረጉ የተለያዩ ቁሳቁሶችን የሚያመርቱ ኩባንያዎች በኢንዱስትሪ ፓርኮች ውስጥ ለማምረት ፍላጎት እንዳላቸው ገልጸዋል፡፡

ኩባንያዎቹ ለማዕድን ማውጣት አገልግሎት የሚውሉ መኪኖችና የሞተር ክፍሎችን እንዲሁም የህክምና ቁሳቁሶችን በኢንዱስትሪ ፓርኮች ለማምረት ነው ፍላጎታቸውን የገለጹት፡፡

የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ አክሊሉ ታደሰ ፥ የኩባንያዎቹን ተወካዮች በፅህፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል፡፡

ኮርፖሬሽኑ ለኢንቨስትመንታቸው እውን መሆን ያልተቋረጠ ድጋፍ እንደሚያደርግም አረጋግጠዋል።

ኮርፖሬሽኑ የሚያቀርባቸውን ኢንቨስትመንት ተኮር አገልግሎቶች፣ በዓለም አቀፍ ደረጃ ገንብቶ የሚያስተዳድራቸውን ኢንዱስትሪ ፓርኮች እንዲሁም የኢንቨስትመንት ማበረታቻዎችና ምቹ ሁኔታዎችን የተመለከቱ ዝርዝር መረጃዎች ለኩባንያዎቹ አቅርበዋል፡፡

ኩባንያዎቹም ስለኢንቨስትመንታቸውና መስራት ስለሚያስቡት ስራ ዝርዝር መረጃዎችን ማቅረባቸውን ከኮርፖሬሽኑ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

በቀጣይም በኢንዱስትሪ ፓርኮች ውስጥ ገብተው ለማምረት የሚያስችላቸውን የቅድመ ኢንቨስትመንት ስራዎች እንደሚያከናውኑ ነው የገለጹት፡፡

#Ethiopia #Belarus #industrialpark #ethiopiainvest

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.