Fana: At a Speed of Life!

በጫሞ ሐይቅ ከሰጠመችው ጀልባ የሰባት ሰዎች አስከሬን ተገኘ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 18፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ቅዳሜ ከሰዓት ከአማሮ ልዩ ወረዳ አልፉጮ አቡሎ ወደ አርባምንጭ ከተማ ስምንት ሰዎችን አሳፍራ በጫሞ ሐይቅ ከሰጠመችው ጀልባ እስካሁን የሰባት ሰዎች አስከሬን ተገኘ፡፡

የጋሞ ዞን ፖሊስ አዛዥ ምክትል ኮማንደር ደግፌ ደበላ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለጹት÷ እስካሁን የሰባት ሰዎች አስከሬን ተገኝቷል።

የአንደኛውን ተሳፋሪ አስከሬን ለማግኘት ተጨማሪ የፍለጋ ስራ እየተሰራ መሆኑንም ገልጸዋል።

አደጋው በደረሰበት ወቅት ጀልባዋ ከተሳፋሪዎቹ በተጨማሪ ከ60 ኩንታል በላይ ዕቃ መጫኗን የዞኑን ፖሊስ ጠቅሰን መዘገባችን ይታወሳል።

የአደጋው መንስኤ ከመጠን በላይ በመጫን የተፈጠረ ሳይሆን እንዳልቀረም ነው የተገለጸው።

ከዚህ ባለፈም በወቅቱ ባልተለመደ ሁኔታ ማዕበል ተከስቶ እንደነበርም ተገልጿል።

በዮሐንስ ደርበው

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.