Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ በዓለም የጉምሩኮች ድርጅት  የህግ ማስከበር ኮሚቴ ስብሰባ እየተሳተፈች ነው

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 20፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ በ43ኛው የዓለም የጉምሩኮች ድርጅት የህግ ማስከበር ኮሚቴ ስብሰባ እየተሳተፈች ትገኛለች፡፡

ለአራት ቀናት በቤልጂየም ዋና ከተማ ብራስልስ እየተካሄደ በሚገኘው ዓለምአቀፍ ስብሰባ ፤ የጉምሩክ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር አቶ ሙሉጌታ በየነ ኢትዮጵያን በመወከል እየተሳተፉ ነው፡፡

በ1983 እ.ኤ.አ የተመሰረተው የዓለም የጉምሩክ ድርጅት የህግ ማስከበር ኮሚቴ ዘንድሮ የተመሰረተበትን  40ኛ ዓመት በተለያዩ ሁነቶች ያከብራል ተብሏል፡፡

በተጨማሪም ድንበር ተሻጋሪ የህገወጥ ንግድ እና ኮንትሮባንድን ለመቀነስ እንዲሁም ለመከላከል በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ምክክር ይደረጋል መባሉን ከጉምሩክ ኮሚሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.