Fana: At a Speed of Life!

ኦ.ቢ.ኤን በምስራቅ አፍሪካ ተደራሽ የሚሆን 2ኛ ቻናል የሙከራ ስርጭት ጀመረ

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 8፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኦሮሚያ ብሮድካስቲንግ ኔትዎርክ (ኦ.ቢ.ኤን) በምስራቅ አፍሪካ ተደራሽ የሚሆን ሁለተኛ ቻናል ዛሬ የሙከራ ሥርጭት ጀምሯል።
ይህ ቻናል ኦ.ቢ.ኤን የምስራቅ አፍሪካ (OBN Horn Of Africa) በሚል ስያሜ እንዲጠራ የክልሉ መንግስት መወሰኑም በምክትል ርእሰ መስተዳድር ማዕረግ የማህበራዊ ክላስተር ኃላፊ እና የድርጅቱ ቦርድ ሰብሳቢ አቶ አዲሱ አረጋ በፌስቡክ ገፃቸው አስታውቀዋል።
 
የቻናሉ ዋነኛ ዓላማ የአፍሪካ ቀንድ ህዝቦችን ማቀራረብ እና ወንድማማችነት ማጠናከር ነዉም ተብሏል።
 
ከዚያም ባለፈ የምስራቅ አፍሪካን ቀጠናዊ ትስስር እዉን ለማድረግ እየተደረገ ያለውን እንቅስቃሴ እውን ከማድረግ አኳያ የኦሮሞ ህዝብ እና የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት የሚጠበቅበትን ሃላፊነት እንዲወጣ ማስቻል ነዉ ይረዳል ተብሏል።
 
ቻናሉ በአፋን ኦሮሞ፣ ኢንግሊዘኛ፣ አረቢኛ፣ በሶማሊኛ፣ በትግርኛ፣ በሱዋሂሊ፣ በአፋርኛ፣ አማርኛ፣ በሲዳሚኛ እና በሌሎች ቋንቋዎች ዜና፣ ፕሮግራሞች እና የመዝናኛ ዝግጅትቶችን እንደሚያሰራጭ ከአቶ አዲሱ አረጋ አስታውቀዋል።

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!

https://t.me/fanatelevision

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.