Fana: At a Speed of Life!

ከንቲባ አዳነች ከኮንራድ ኤን ሂልተን ፋውንዴሽን ከፍተኛ አመራሮች ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 10፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ከኮንራድ ኤን ሂልተን ፋውንዴሽን ከፍተኛ አመራሮች ጋር ተወያዩ፡፡

ከንቲባ አዳነች በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ÷ መዲናዋን ለሕጻናት ምቹ በማድረግ ምርጥ የአፍሪካ ከተማ እንድትሆን በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ በትብብር ለመስራት መምከራቸውን ገልጸዋል፡፡

አዲስ አበባ ከተማ የሁሉም ከተማ እንድትሆን፣ ለሕጻናት ሁለንተናዊ ዕድገት ብሎም እንክብካቤ እንድትመች ለማድረግ በሚከናወነው ጥረትም በቀጣይነት ድጋፍ ለማድረግ የፋውንዴሽኑ ከፍተኛ አመራሮች ቃል መግባታቸውንም ነው ከንቲባ አዳነች ያመላከቱት፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.