Fana: At a Speed of Life!

ሳዲዮ ማኔ የ350 ሺህ ዩሮ የገንዘብ ቅጣት ተላለፈበት

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 11፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የቀድሞ የሊቨርፑል ኮከብ ሳዲዮ ማኔ የ350 ሺህ ዩሮ የገንዘብ ቅጣት ውሳኔ የተላለፈበት መሆኑን ክለቡ አስታውቋል፡፡

ማኔ የቡድን አጋሩን ሌሮይ ሳኔ በመልበሻ ክፍል ውስጥ በቡጢ በመደብደቡ ነው  የገንዘብ ቅጣቱ የተላለፈበት፡፡

የተጣለው የገንዘብ ቅጣትም በክለቡ ታሪክ ከፍተኛው መሆኑን  መረጃዎች ያመላክታሉ፡፡

በፈረንጆቹ 2012 የክለቡ ተጫዋች ፍራንክ ሪቤሪ በተመሳሳይ አሪየን ሮበንን በመደባደቡ ምክንያት 50 ሺህ ዩሮ የገንዘብ ቅጣት ተላለፎበት እንደነበር የሚታወስ ነው፡፡

የባይርሙኒኩ አሰልጣኝ ቶማስ ቱኸል መሰል የዲሲፕሊን ግድፈቶችን ክለቡ እንዳማይታገስ ገልጸው÷ በሳዲዮ ማኔ እና በሌሮይ ሳኔ መካከል የተፈጠረው አለመግባባት መፈታቱን ጠቁመዋል፡፡

“ሳዲዮ ማኔን ለረጅም ጊዜ ሳውቀው እንደዚህ አይነት ባህርይ አልነበረውም” ያሉት አሰልጣኙ÷ በቅርቡ ወደ ልምምድ ሜዳ እንደሚመለስ እምነት አለኝ ብለዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.