Fana: At a Speed of Life!

አርባምንጭ ከተማ ከኢትዮጵያ ቡና አቻ ተለያዩ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 11፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አርባምንጭ ከተማ ከኢትዮጵያ ቡና 1 አቻ ተለያዩ፡፡

ጎሎቹን ተመስገን ደረሰ ለአርባምንጭ ከተማ  እንዲሁም ሞሀመድ ናስር ለኢትዮጵያ ቡና አስቆጥረዋል፡፡

ክለቦቹ ነጥብ መጋራታቸውን ተከትሎ የደረጃ ለውጥ ሳያደርጉ በነበሩበት 12ኛ እና 7ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል፡፡

በሌላ የጨዋታ መርሐ ግብር ምሽት 12 ሰዓት ለዋንጫ የሚፎካከረው ባሕርዳር ከተማ ከለገጣፎ ለገዳዲ ጋር የሚያደርጉት ጨዋታ ይጠበቃል፡፡

ባሕርዳር ከተማ ከለገጣፎ ለገዳዲ ያደረገውን ጨዋታ 3 ለ 1 በማሸነፍ የዋንጫ ተፎካካሪነቱን አጠናክሯል፡፡

የባሕርዳር ከተማን ጎሎች ፋሲል አስማማው፣ አለልኝ አዘነ እና የአብስራ ተስፋየ አስቆጥረዋል፡፡

የለገዳዲ ለገጣፎን ብቸኛ ጎል ደግሞ ጋብሬል አሕመድ ነው ያስቆጠረው፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.