Fana: At a Speed of Life!

ከንቲባ አዳነች አቤቤ ለዒድ አልፈጥር በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 12፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ለ1 ሺህ 444ኛው የዒድ አል ፈጥር በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

ከንቲባዋ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስላለፉት መልዕክት÷ታላቁ የረመዳን ወር መተዛዘን የሚጎለብትበት፣ ለሌሎች ማዘን የሚልቅበት፣ አንድነት እና ወንድማማችነት የሚጠነክርበት ነው ብለዋል፡፡

መላው የእስልምና እምነት ተከታዮች በዚህ የእዝነት ወር ሲተገብሩት የነበረውን መልካም ምግባር ከዒድ በኋላም አጠናክረው አንዲቀጥሉ አደራ ብለዋል፡፡

ህዝበ ሙስሊሙ በበዓሉ ወቅት እንደ ከዚህ ቀደሙ ሁሉ አቅመ ደካሞችን በማሰብ እንዲያሳልፍም ጥሪ አቅርበዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.