Fana: At a Speed of Life!

አቶ ደመቀ መኮንን የአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 15፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን የአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ማይክ ሃመር ጋር ተወያይተዋል፡፡

በውይይታቸውም ኢትዮጵያ እና አሜሪካ የቆየ ግንኙነታቸውን ይበልጥ ማጠናከር በሚችሉበት ሁኔታ ላይ  መክረዋል፡፡

በቀጣናው የሚስተዋሉ የጸጥታ ችግሮችን መፍታት በሚቻልባቸው መንገዶች ላይ መወያየታቸውንም የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡

አቶ ደመቀ በሱዳን የተፈጠረውን ግጭት በሀገሪቱ ሕዝቦች ጥረት እንዲፈታ ኢትዮጵያ ገንቢ ሚና  እየተጫዎተች መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ማይክ ሃመር በበኩላቸው÷አሜሪካ በኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላም እና ልማት እንዲረጋገጥ የምታደርገው ጥረት አጠናክር ትቀጥላለች ብለዋል፡፡

በቀጣናው የሚስተዋሉ ችግሮች ፈታኝ እየሆኑ መምጣታቸውን ያነሱት ልዩ መልዕክተኛው÷ችግሩን ለመፍታትም የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ የተቀናጀ ጥረት እንዲያደርግ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.