Fana: At a Speed of Life!

የታዳሽ ሃይል ኢንቨስትመንት ፎረም  እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 17፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የታዳሽ ሃይል ኢንቨስትመንት ፎረም በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው፡፡

ፎረሙን የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ከአፍሪካ ኢነርጂ ጋር በመተባበር እንዳዘጋጁት ተገልጿል፡፡

የውሃ እና ኢነርጂ ሚኒስትር ሀብታሙ ኢተፋ(ዶ/ር ኢ/ር)÷የኢትዮጵያ ህዝብ የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦትን እንዲያገኝ ለማስቻል መንግስት የግሉን ዘርፍ በማሳተፍ ያለውን አቅም በመለየት፣ የፖሊሲና ሕግ ማዕቀፎችን በማዘጋጀት ባለሃብቶችን ለመሳብ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ከታዳሽ ኃይል ዘርፎች በጂኦተርማል፣ ከንፋስ እና ከፀሀይ ኃይል ለማመንጨት የተለያዩ የውጭ ድርጅቶች ፍላጎት ማሳየታቸውንና ወደ ስራ ለመግባትም በእንቅስቃሴ ላይ እንዳሉም ተጠቁሟል፡፡

መድረኩ ለሁለት ቀናት የሚቆይ ሲሆን÷ ኢትዮጵያ በታዳሽ ኃይል ዘርፍ ያላትን እምቅ አቅም በስፋት ለማስተዋወቅ ያስችላታል መባሉን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል፡፡

ኢትዮጵያ እና ታንዛኒያ በታዳሽ ኃይሉ ዘርፍ እምቅ አቅም እንዳላቸው በመድረኩ የተጠቀሰ ሲሆን÷ ይህን አቅም አሟጦ ለመጠቀም በትብብር መስራት ይጠይቃል ተብሏል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.