Fana: At a Speed of Life!

አቶ ደመቀ መኮንን በአቶ ግርማ የሺጥላ ህልፈት የተሰማቸውን ሃዘን ገለጹ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 20፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን በአማራ ክልል ብልጽግና ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ ግርማ የሺጥላ ህልፈት የተሰማቸውን ሃዘን ገልጸዋል፡፡
 
አቶ ደመቀ በሃዘን መግለጫቸው ÷“ወንድማችን አቶ ግርማ የሺጥላ በስራ ላይ እያሉ በታጠቁ ሃይሎች በተፈጸመባቸው ጥቃት መገደላቸውን ስሰማ ከፍተኛ እና ጥልቅ የሆነ ሀዘን ተሰምቶኛል” ብለዋል።
 
አቶ ግርማ እና የግል ጠባቂዎቻቸው ላይ የተፈጸመው ድርጊት ፍጹም ተቀባይነት የሌለው፣ የህዝባችንን እሴት የማይመጥን ነውር እና ህገወጥ ድርጊት ነው ሲሉም ገልጸዋል።
 
አቶ ግርማ የህዝብ ህይወት እንዲሻሻል የተሰጠውን ህዝባዊ ኃላፊነት እየተወጣ እንደነበር አውስተው÷ ህልፈቱ ለመላው ለክልላችን እና ሀገራችን ህዝቦች ከፍተኛ ጉዳት ነው ብለዋል፡፡
 
መንግስት ይህን ድርጊት የፈጸሙ አካላትን ለህግ በማቅረብ ተጠያቂ እንዲሆኑ እንደሚሰራም አረጋግጠዋል፡፡
 
አቶ ደመቀ ለሟች ቤተሰቦች፣ ወዳጅ ዘመዶቹ እና ለመላው ህዝብም መጽናናትን ተመኝተዋል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.