Fana: At a Speed of Life!

ከ63 ሺህ በላይ መምህራንና የዘርፉ አካላትን ያሳተፈ ውይይት በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 20፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ከ63 ሺህ በላይ መምህራንና የዘርፉ አካላትን ያሳተፈ ውይይት በአዲስ አበባ ከተማ እየተካሄደ ነው፡፡

የውይይት መድረኩ በ77 ክላስተር ማዕከላት እየተካሄደ ሲሆን÷ በዚህም ከ1 ሺህ 368 በላይ አወያዮች መሳተፋቸው ተገልጿል፡፡

የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዘላለም ሙላቱ (ዶ/ር) በሰጡት መግለጫ ÷ የውይይትመድረኩ ለተማሪዎችና ለትምህርት ማህበረሱብ ሊጠቅሙ በሚችሉ አጀንዳዎች ላይ እንደሚያተኩር ተናግረዋል፡፡

ባለፉት ሶስትና አራት ዓመታት በትምህርቱ ዘርፍ የታዩ ለውጦችን የበለጠ አሻሽሎና አጎልብቶ ማስቀጠል በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ እንደሚመከረም አንስተዋል።

የውይይት መድረኩ ከዛሬ ጀመሮ ለተከታታይ አራት ቀናት የሚካሄድ ሲሆን÷በቀጣይ እሑድ ከሁሉም ክፍለ ከተሞች ጋር የጋራ መግባባት ለመፍጠር ምክክር እንደሚደረግ ተጠቁሟል።

ሰኞ በሚኖረው መርሐ-ግብር 5 ሺህ የሚደርሱ መምህራን ከከንቲባ አዳነች አቤቤ እና ከከፍተኛ አመራሩ ጋር በሚደረጉ ውይይቶች ላይ እንደሚሳተፉም ተገልጿል፡፡

በይስማው አደራው

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.