Fana: At a Speed of Life!

የአፍሪካ ከ18 እና ከ20 አመት በታች አትሌቲክስ ሻምፒዮና ዛሬ ይጠናቀቃል

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 25፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በዛምቢያ ንዶላ ሲካሄድ የቆየው 2ኛው የአፍሪካ ከ18 እና ከ20 ዓመት በታች አትሌቲክስ ሻምፒዮና ዛሬ ይጠናቀቃል፡፡

በሻምፒዮናው መዝጊያ ዕለት የቡድን 5 ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በሁለቱም ጾታዎች በተለያዩ ርቀቶች ይሳተፋሉ፡፡

አሁን ላይ ከ18 አመት በታች የሴቶች 5 ሺህ ሜትር የእርምጃ ውድድር  አበቡ አያሌው ሁለተኛ በመሆን የብር ሜዳሊ ለሀገሯ አስገኝለች፡፡

ኢትዮጵያ እስከ አሁን በሻምፒዮናው 6 የወርቅ፣ 8 የብር እና 3 የነሐስ ሜዳሊያዎችን ሰብስባለች፡፡

17 ሜዳሊያዎችን በማገኘት ከተሳታፊ ሀገራት ሁለተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.