Fana: At a Speed of Life!

የቀጨኔ ዘላቂ ማረፊያ አጥር ግንብ ተደርምሶ የ2 ሰዎች ህይወት አለፈ

 

አዲስ አበባ ፣ ሚያዝያ 30 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ ጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 4 የቀጨኔ ዘላቂ ማረፊያ አጥር ግንብ አጠገብ በተለምዶ በግ ተራ በሚባለው ቦታ በደረሰ የግንብ መደርመስ አደጋ የ2 ሰዎች ህይወት አለፈ።

በደረሰው አደጋ ጉዳት የደረሰባቸው ሌሎች 4 ሰዎች አቤት ሆስፒታል እና መነን ጤና ጣቢያ መወሰዳቸውን በወረዳው የቀጨኔ ፖሊስ ጣቢያ ወንጀል ምርመራ ማስተባበሪያ ኃላፊ ኢንስፔክተር ተስፋዬ እሸቱ ገልጸዋል።

በአካባቢው በደረሰው የመደርመስ አደጋ ቁጥራቸው ለጊዜው በውል ያልታወቁ በግ እና ፍየሎች መሞታቸው ተገልጿል።

የአደጋ ጊዜ ሠራተኞች በደረሰው አደጋ የተጎዱ ሰዎችን እያገዙ እና የነፍስ አድን ሥራ እየሠሩ እንደሚገኝም ተጠቅሷል።

የአዲስ አበባ እሳት እና አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን የሕዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ ንጋቱ ማሞ፤ ቀጣይ ክረምትን ተከትሎ ሊያጋጥሙ የሚችሉትን አደጋዎችን በመገመት ዜጎች ጥንቃቄ እንዲያደርጉ መልዕክት ማስተላለፋቸውን ከጉለሌ ክፍለ ከተማ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.