Fana: At a Speed of Life!

በአትላንታ ከንቲባ የተመራ ልዑክ አዲስ አበባ ገባ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 3፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በአትላንታ ከተማ ከንቲባ አንድሬ ዲከንስ የተመራ ልዑክ ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት አዱስ አበባ ገብቷል።

ቡድኑ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርስ የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ አቶ ጃንጥራር አባይ፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ መስፍን ጣሰው እንዲሁም ሌሎች የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች አቀባበል አድርገውለታል።

ልዑኩ በአዲስ አበባ ቆይታው ሁለቱ ከተሞች በጋራ በሚሰሩባቸው አጀንዳዎች ዙሪያ ከከንቲባ አዳነች አቤቤ ጋር ውይይት እንደሚያደርግ የከንቲባ ጽህፈት ቤት መረጃ ያመላክታል።

ከዚህ ባለፈም በከተማዋ የተሰሩ ስራዎችን ተዘዋውሮ እንደሚጎበኝም ይጠበቃል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.