Fana: At a Speed of Life!

ከአትክልትና ፍራፍሬ ምርቶች የወጪ ንግድ 514 ሚሊየን ዶላር በላይ ገቢ ተገኘ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 8፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በዘጠኝ ወራት ውስጥ ከአትክልትና ፍራፍሬ ምርቶች የወጪ ንግድ 514 ነጥብ 1 ሚሊየን ዶላር ገቢ መገኘቱን የግብርና ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

ሚኒስቴሩ በዘጠኝ ወር ሪፖርቱ እንዳስታወቀው በ2015 በጀት ዓመት ባለፉት ዘጠኝ ወራት 215 ሺህ 884 ነጥብ 75 ቶን የሆርቲካልቸር ምርቶችን ወደ ውጪ በመላክ 514 ነጥብ 1 ሚሊየን ዶላር ማግኘት ተችሏል፡፡

እንደ ሚኒስቴሩ መረጃ በምርት ዓይነት ሲታይ በአበባ ምርት 444 ሚሊየን ዶላር በአትክልትና ፍራፍሬ ምርት ደግሞ 70 ነጥብ 3 ሚሊየን ዶላር ገቢ ተገኝቷል።

የወጪ ንግድን በመጠንና በገቢ ለማሳደግ ዘርፈ ብዙ ስራዎች መሰራታቸውም በሪፖርቱ ተመላክቷል፡፡

በሆርቲካልቸር ዘርፍ የተገኘው የዘጠኝ ወራት አፈጻጸም ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የ15 ነጥብ 7 በመቶ የገቢ ጭማሪ ማሳየቱን ሚኒስቴሩ በሪፖርቱ አስታውቋል።

በመኸር ወቅት በአብዛኞቹ ክልሎች የነበረው ምቹ የዝናብ ስርጭት በተገቢው ለእርሻ ተግባር መጠቀም በመቻሉ የ2014/15 የመኸር ሰብል በመልካም ሁኔታ እንዲገኝ አስችሏል መባሉን ኢፕድ ዘግቧል፡፡

የቅድመና የድህረ-ምርት ሜካናይዜሽን መሳሪያዎች አቅርቦት ማነስ፣ በሽታን የሚቋቋሙ የሰብል ቴክኖሎጂዎች አለመኖር፣ የዕጽዋት በሽታ፣ በሰው ኃይልና በሎጂስቲክስ የተጠናከረ መዋቅር በክልሎች አለመኖር በሰብልና ሆልቲካልቸር ልማት ተግዳሮቶች መሆናቸውንም ሪፖርቱ አመላክቷል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.