Fana: At a Speed of Life!

በአደጋ ስጋት ውስጥ ያሉ የቆሼ ነዋሪዎች በአስቸኳይ እንደሚነሱ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 11፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ በተለምዶ ቆሼ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ የአደጋ ስጋት ተጋላጭ የሆኑ ነዋሪዎችን ከቦታው የማንሳት ስራ በአጭር ቀናት ውስጥ እንደሚጠናቀቅ ተገለጸ፡፡

በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ጥራቱ በየነ የአደጋ ስጋት በሆነው የደረቅ ቆሻሻ ማከማቻ ቦታ አካባቢ የሚኖሩ ነዋሪዎችን የማንሳት ሂደቱ ያለበትን ደረጃ ከሌሎች የካቢኔ አባላት ጋር በመሆን ጎብኝተዋል።

ከዚህ ቀደም አጣዳፊ የአደጋ ስጋት ያለባቸው ነዋሪዎች መነሳታቸውን ያወሱት አቶ ጥራቱ ቀሪ 25 ነዋሪዎችም ተገቢው ካሳና ምትክ ቦታ ተዘጋጅቶላቸው በአጭር ጊዜ ውስጥ ይነሳሉ ብለዋል።

በአካባቢው በህገ ወጥ መንገድ ላስቲክ ወጥረው የሚኖሩ ከ300 በላይ ነዋሪዎችም በአደጋ ስጋት ያሉ በመሆኑ በፍጥነት ከስጋት ነጻ እንዲሆኑ የማድረግ ስራም በትኩረት ይሰራል ነው ያሉት አቶ ጥራቱ።

በወንዝ ዳርቻዎችና እንደዚህ አይነት የአደጋ ስጋት ያለባቸው ቦታዎች ላይ የሚኖሩ ነዋሪዎች የአደጋ ተጋላጭነትን ለመቀነስ የሚሰራውን ስራ በመደገፍ ሊተባበሩ እንደሚገባ ጥሪ መቅረቡን ከእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

የደረቅ ቆሻሻ በሚከማችበት ቆሼ አካባቢ ከዚህ በፊት ተደርምሶ በሰውና በንብረት ላይ ከባድ ጉዳት ማስከተሉ ይታወሳል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.