አዲስ አበባ፣ ግንቦት 20፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በቱርክ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ሬሲፕ ጣይብ ኤርዶኻን በድጋሚ ተመረጡ።
በመጀመሪያ ዙር ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ከ50 በመቶ በላይ ያገኘ እጩ ባለመኖሩ ነበር ዛሬ ሁለተኛ ዙር ድምፅ አሰጣጥ የተካሄደው።
እስካሁን 97 በመቶ ድምፅ የተቆጠረ ሲሆን፥ 53 ነጥብ 4 በመቶ ድምፅ በማግኘት በድጋሚ መመረጣቸውን አረጋግጠዋል።
ሪፐብሊካን ፒፕልስ ፓርቲ ሊቀመንበር እና ከስድስት ፓርቲዎች ጥምረት ኔሽን አሊያንስ የጋራ እጩ ከማል ኪሊዳሮግሉን ደግሞ 47 ነጥብ 9 በመቶ አግኝተዋል ተብሏል።