Fana: At a Speed of Life!

በአማራ ክልል  ከበጋ ስንዴ ልማት ከ6 ነጥብ 4 ሚሊየን ኩንታል በላይ ምርት መሰብሰቡ ተገለፀ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 27፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ)በአማራ ክልል በበጋ ወቅት በመስኖ ከለማ ስንዴ ከ6 ነጥብ 4 ሚሊየን ኩንታል በላይ ምርት መሰብሰቡን የክልሉ ግብርና ቢሮ አስታወቀ።

በክልሉ ደቡብ ወሎ ዞን መቅደላ ወረዳ በበጋ ወቅት በመስኖ ለምቶ ለመሰብሰብ የደረሰ የስንዴ ሰብል ዛሬ ተጎብኝቷል።

በጉብኝቱ ላይ የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ ኃላፊ ኃይለማሪያም ከፍያለው(ዶ/ር) በዘንድሮ የበጋ ወቅት ብቻ 213 ሺህ ሄክታር መሬት ላይ ስንዴ በመስኖ መልማቱን ገልጸዋል።

በአሁኑ ወቅት ሰብሉ በመድረሱ እየተሰበሰበ መሆኑን የገለጹት ቢሮ ኃላፊው እስካሁንም ከ187 ሺህ ሄክታር በሚበልጥ መሬት ላይ የለማ ስንዴ ታጭዶ መሰብሰቡን ተናግረዋል።

እንደ ኃላፊው ገለጻ እስካሁን ከ6 ነጥብ 4 ሚሊየን ኩንታል በላይ ምርት የተገኘ ሲሆን÷ቀሪውን የደረሰ ሰብል በፍጥነት ከማሳ ላይ አንስቶ በመውቃት ምርቱን አጠናቆ ለማስገባት በቅንጅት እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡

አርሶ አደሩም የደረሰውን ሰብል ፈጥኖ በማንሳት ማሳውን ለመጪው የመኸር እርሻ እንዲያዘጋጅ ማሳሰባቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.