Fana: At a Speed of Life!

በክልሉ በበልግ እርሻ ከ317 ሺህ ሄክታር በላይ ማሳ መልማቱ ተገለፀ

 

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 29 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ)በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል በበልግ እርሻ ከ317 ሺህ ሄክታር በላይ ማሳ በተለያዩ ሰብሎች መልማቱን የክልሉ ግብርና ቢሮ አስታወቀ።

የቢሮው ምክትል የእርሻ ዘርፍ ሃላፊ አቶ አሸናፊ ክንፉ÷ በበልግ የለማ ሰብል በአሁኑ ወቅት በተሻለ ቁመና ላይ እንደሚገኝ በመስክ ምልከታ መረጋገጡን ገልጸዋል።

በበልግ ወቅት በዘር ተሸፍኖ እየለማ ካለው ከ317 ሺህ ሄክታር በላይ ማሳም ከ11 ሚሊየን ኩንታል በላይ ምርት ይሰባሰባል ተብሎ እንደሚጠበቅ ጠቅሰዋል።

በክልሉ በበልግ እርሻ በቆሎ በብዛት እንደሚመረት ገልጸው አሁን እየለማ ካለው አጠቃላይ ማሳም 75 በመቶ የሚሆነው በቆሎ መሆኑን መናገራቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.