Fana: At a Speed of Life!

ኮርፖሬሽኑ የግንባታ ግብዓት ማምረቻ ማሽን ተከላ ግንባታ ስራን አስጀመረ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 30፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን የግንባታ ግብዓት ማምረቻ ማሽን ተከላ ሥራን ለማከናወን የሚያስችለውን የግንባታ ፕሮጀክት አስጀምሯል፡፡
 
ፕሮጀክቱ በኮንስትራክሽን ዘርፉ የሚስተዋለውን የግብዓት አቅርቦት እጥረትን የሚያቃልሉ የኮንክሪት ውሕድ እና ብሎኬት ማምረቻ ማሽን ተከላ ለማከናወን የሚያስችል መሆኑ ተገልጿል፡፡
 
የፕጀክቱን ግንባታ ሒደት እና ያለበትን ደረጃ የኮርፖሬሽኑ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ረሻድ ከማልን ጨምሮ የማኔጅመንት አባላት ጎብኝተዋል፡፡
 
አቶ ረሻድ ከማል ÷የግንባታ ግብዓት ማምረቻ ማዕከሉ የማሽን ተከላው ሲጠናቀቅ ኮርፖሬሽኑ ለሚያከናውናቸው ሰፋፊ የቤት ልማት ፕሮግራሞች አስተማማኝ የግብዓት አቅርቦት መፍጠር ያስችላል ብለዋል፡፡
 
በተጨማሪም ሌሎች በግንባታው ዘርፍ ለተሰማሩ አልሚዎች በተመጣጣኝ ዋጋ ምርቶቹን በማቅረብ የቤት ልማት ዘርፉን እድገት ለማሳላጥ ያስችላል ነው ያሉት፡፡
 
ማዕከሉ በ3 ነጥብ 2 ሄክታር ቦታ ስፋት ላይ ያረፈ ሲሆን÷ ማሽን ተከላው ሲጠናቀቅ በቀን ከ2 ሺህ 400 በላይ ሜትር ኪዩቢክ የኮንክሪት ውህድ የማምረት ዓቅም ይኖረዋል ተብሏል፡፡
 
የብሎኬት ማምረቻ ማሽኑም በቀን የተለያዩ መጠን ያላቸውን ከ60 ሺህ በላይ ብሎኬቶችን የማምረት ዓቅም እንዳለው መገለጹን የኮርፖሬሽኑ መረጃ ያመላክታል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.