Fana: At a Speed of Life!

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን የተላለፉ 9 ግለሰቦች በገንዘብ ተቀጡ

አዲስ አበባ ፣ ሚያዚያ 21 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅን በመተላለፍ የተከሰሱ 9 ግለሰቦች በገንዘብ ተቀጡ።

ግለሰቦቹ ሚያዚያ 9 ቀን 2012 ዓ.ም በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ በጣም ጠባብ በሆነ አንድ ክፍል ቤት ውስጥ ጫት ሲቅሙ የተያዙ ሲሆን በዚህ መሰረት አስቸኳይ ጊዜ አዋጅንና አዋጁን ለማስፈፀም የወጣውን ደንብ በመተላለፍ ጫት በማስቃምና ከአራት ሰው በላይ በመሆን በመሰብሰባቸው የተነሳ ተከሰው ፍርድ ቤት ቀርበዋል።

ዐቃቤ ሕግ በክፍለ ከተማው ፖሊስ መመሪያ ምርመራ መዝገብ መሰረት የሰው እና የሰነድ ማስረጃዎችን በማጠናከር ለፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አቅርቧል።

ፍርድ ቤቱም ጉዳዩን መርምሮ ተከሳሾች የወንጀል ድርጊቱን መፈፀማቸውን በዝርዝር በማመናቸው ሚያዚያ 19 ቀን 2012 ዓ.ም በዋለው ችሎት እያንዳንዳቸው 3 ሺህ መቀጮ እንዲቀጡ ወስኗል።

በተያያዘም በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ 78 ሰዎች የኮቪድ 19 ቫይረስን ለመቆጣጠር የወጣውን አዋጅ በመተላለፍ በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተደረገባቸው እንደሚገኝ ከጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.