Fana: At a Speed of Life!

ፋሲል ከነማ እና ኢትዮጵያ ቡና ነጥብ ተጋሩ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 28፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በ30ኛ ሳምንት የቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ፋሲል ከነማ እና ኢትዮጵያ ቡና 0 ለ 0 ተለያይተዋል፡፡
የቡድኖቹ ጨዋታ በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም 9፡00 ላይ ተከናውኗል፡፡
ቡድኖቹ ነጥብ መጋራታቸውን ተከትሎም በግብ ክፍያ ተበላልጠው በእኩል 43 ነጥብ 4ኛ እና 5ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል፡፡
የ30 ኛ ሳምንት የጨዋታዎች መርሐ ግብር ማምሻውን ሲቀጥል 1፡00 ላይ ሲዳማ ቡና መውረዱን ካረጋገጠው ኢትዮ ኤሌክትሪክ ጋር ይገናኛሉ፡፡

 

በተመሳሳይ 12፡00 ላይ በተካሄደ የ30ኛ ሳምንት የጨዋታ መርሐ ግብር መውረዱን ያረጋገጠው ኢትዮ ኤሌክትሪክ ሲዳማ ቡናን 2 ለ 1 አሸንፏል፡፡

አብዱራህማን ሙባረክ የኢትዮ ኤሌክትሪክን ሁለት ጎሎች ሲያስቆጥር÷ የሲዳማ ቡናን ብቸኛ ጎል ደግሞ ፍሊፕ አጃህ አስቆጥሯል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.