Fana: At a Speed of Life!

በመዲናዋ ለ2 ሺህ 904 ባለሃብቶች አዲስ የኢንቨስትመንት ፈቃድ ተሰጠ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 30፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በ2015 ዓ.ም ለ2 ሺህ 904 ባለሃብቶች አዲስ የኢንቨስትመንት ፈቃድ መስጠቱን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኢንቨስትመንት ኮሚሽን አስታወቀ።

የአልሚዎችን ፍላጎት መሰረት በማድረግም ኮሚሽኑ የኢንቨስትመንት ለውጥ ማሻሻያ ሥራ ማከናወኑን ገልጿል፡፡

በተጨማሪም ለ1 ሺኅ 854 የኢንቨስትመንት እድሳት እና ለ232 የኢንቨስትመንት ማስፋፊያ ፈቃድ መስጠቱን ነው ያመላከተው፡፡

እንዲሁም 98 ምትክ ፈቃድ መሰጠቱን የኮሚሽኑ መረጃ ያመላክታል፡፡

ኮሚሽኑ ለአልሚዎች ከሰጠው ልዩ ልዩ አገልግሎቶች 26 ነጥብ 4 ሚሊየን ብር የሰበሰበ ሲሆን፥ ተገልጋዮች ባሉበት ሆነው አገልግሎቶችን በኦንላይን እንዲያገኙ ማድረጉንም አስታውቋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.