Fana: At a Speed of Life!

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ከ2 ቢሊየን ብር በላይ ላስመዘገቡ አልሚዎች ፈቃድ ተሰጠ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 23፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ከ2 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር በላይ ካፒታል ላስመዘገቡ አልሚዎች ፈቃድ መስጠቱን የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ኢንቨስትመንት ቢሮ ገለጸ፡፡

ለ166 ፕሮጀክቶች ፈቃድ ለመስጠት ታቅዶ÷ በግብርና 67፣ በአገልግሎት 53 እና በኢንዱስትሪ 21 በአጠቃላይ ለ141 ፕሮጀክቶች ፈቃድ በመስጠት የዕቅዱን 84 ነጥብ 9 በመቶ ማሳካት መቻሉን ቢሮው አስታውቋል፡፡

ፈቃድ በተሰጠባቸው ፕሮጀክቶች 2 ሺህ 892 ቋሚ እና 79 ሺህ 335 ጊዜያዊ የሥራ ዕድል መፈጠሩን ነው ቢሮው ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ያስታወቀው፡፡

ከመሬት ዝግጅት አንጻርም በበጀት ዓመቱ 32 ሺህ 170 ሄክታር ለኢንቨስትመንት ዝግጁ ማድረግ ተችሏል ብሏል፡፡

በዮሐንስ ደርበው

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.