Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያና ደቡብ ኮሪያ የቀጥታ አየር በረራ ቁጥራቸውን ከፍ ለማድረግ ተስማሙ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 24፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵና ደቡብ ኮሪያ በሀገራቱ መካከል ያለውን የቀጥታ አየር በረራ ቁጥር ከፍ ለማድረግ ስምምነት ላይ ደርሰዋል፡፡

በሀገራቱ መካከል በሳምንት ሰባት የነበረውን የቀጥታ አየር በረራ ቁጥር ወደ ዘጠኝ ለማሳደግ ስምምነት ላይ መድረሳቸውን የደቡብ ኮሪያ የመሬት፣ መሠረተ ልማትና ትራንስፖርት ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

ይህም የህዝብ ለህዝብ ግንኙነቱን ይበልጥ ለማሳደግ እንደሚረዳ ነው ሚኒስቴሩ ያስታወቀው፡፡

ከኢትዮጵያ ሲቪል አቬየሽን ባለስልጣን ጋር በተገባው ስምምነት መሰረት በአሁኑ ወቅት በአገልግሎት ላይ ከሚገኙት አራት የመንገደኞች እና ሶስት የካርጎ ሳምንታዊ በረራዎች በተጨማሪ ሁለት የመንገደኞች በረራ እንደሚጨመር ተገልጿል።

ኢትዮጵያ ወደ ደቡብ ኮሪያ ቀጥታ በረራ የምታደርግ ብቸኛዋ አፍሪካዊት ሀገር መሆኗ የሚታወቅ ነው፡፡

በርካታ የደቡብ ኮሪያ መንገደኞች በኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ሌሎች አፍሪካ ሀገሮች ለመጓዝ የኢትዮጵያ አየር መንገድን እንደሚመርጡ ዮንሃፕ የተባለው የዜና ምንጭ ዘግቧል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.