Fana: At a Speed of Life!

ሃገራት ገደቦች መላላት መጀመራቸውን ተከትሎ የኮሮና ቫይረስ ሁለተኛ ዙር ይስፋፋል የሚል ስጋት አሳድሯል

አዲስ አበባ ፣ ሚያዚያ 30 ፣2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ሃገራት የጣሉትን ገደብ ማላላት መጀመራቸውን ተከትሎ የኮሮና ቫይረስ ሁለተኛ ዙር ይስፋፋል የሚል ስጋት አሳድሯል።

በአሜሪካ የተወሰኑ ግዛቶችና የአውሮፓ ሃገራት የተወሰኑ አገልግሎት መስጫ ድርጅቶችና ተቋማት ተከፍተው አገልግሎት እንዲሰጡ ማድረግ ጀምረዋል።

ምግብ ቤቶች፣ የተዘጋጁ ምግብና መጠጥ መሸጫና ማከፋፈያዎች፣ የውበት ሳሎኖችና ካፍቴሪያዎች በተወሰኑ ሃገራት አገልግሎት እየሰጡ ነው።

በቻይና ጀርመን ደግሞ ትምህርት ቤቶች ማስተማር ጀምረዋል።

የጤና ሃላፊዎችና ባለሙያዎችም አሁን ላይ ሃገራት የቫይረሱን ስርጭት ለመግታት ጥለውት የነበረውን እገዳ ማላላት መጀመራቸው ቫይረሱ ሁለተኛ ዙር በመዛመት ከፍተኛ ጉዳት እንዲያደርስ ሊያደርገው ይችላል እያሉ ነው።

እስካሁን ዓለም ላይ በቫይረሱ ሳቢያ 269 ሺህ ሰዎች ለህልፈት መዳረጋቸውን የጆን ሆፕኪንስ ዩኒቨርሲቲ መረጃ ያመላክታል።

ከዚህ ውስጥ በአሜሪካ ብቻ ከ75 ሺህ በላይ ሰዎች ለህልፈት ሲዳረጉ ከ1 ነጥብ 2 ሚሊየን በላይ ሰዎች ደግሞ ቫይረሱ ተገኝቶባቸዋል።

ምንጭ፦ አልጀዚራ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.