Fana: At a Speed of Life!

ዛሬ ምሽት በሴቶች 10 ሺህ ሜትር የፍፃሜ ሩጫ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ይጠበቃሉ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 13፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በሃንጋሪ ቡዳፔስት እየተካሄደ በሚገኘው 19ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ዛሬ ምሽት በሚካሄደው የሴቶች 10 ሺህ ሜትር የፍፃሜ ሩጫ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ለአሸናፊነትከፍተኛ ግምት ተሰጥቷቸዋል።

በውድድሩ በአሜሪካ ኦሬጎን በተካሄደው 18ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና በርቀቱ የወርቅ ሜዳሊያ ያገኘችው አትሌት ለተሰንበት ግደይ እንዲሁም ጉዳፍ ፀጋይ፣ እጅጋየሁ ታዬ እና ለምለም ኃይሉ ኢትዮጵያን ወክለው ይወዳደራሉ።

ውድድሩ ዛሬ ምሽት በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር 3 ሰዓት ከ55 ላይ መካሄድ ይጀምራል።

ቀን ላይ በተካሄደው የ3 ሺህ ሜትር መሠናክል ወንዶች ማጣሪያ ኢትዮጵያን ወክለው የተወዳደሩት አትሌት ለሜቻ ግርማና ጌትነት ዋለ ለፍጻሜ አልፈዋል፡፡

እንዲሁም በሴቶች 1 ሺህ 500 ሜትር ማጣሪያ ኢትዮጵያን ወክለው የተወዳደሩት አትሌቶች ሂሩት መሸሻ፣ ብርቄ ኃየሎምና ድርቤ ወልተጂ ወደ ግማሽ ፍጻሜ ማለፋቸው ይታወቃል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.