Fana: At a Speed of Life!

250 ሚሊየን አፍሪካውያን በአንድ አመት በኮሮና ቫይረስ ሊያዙ ይችላሉ – የዓለም ጤና ድርጅት

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 7 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የዓለም ጤና ድርጅት 250 ሚሊየን አፍሪካውያን በአንድ አመት ውስጥ በኮሮና ቫይረስ ሊያዙ እንደሚችሉ አስጠነቀቀ።

የዓለም ጤና ድርጅት ተመራማሪዎች በአንድ አመት ጊዜ ውስጥ ሩብ ቢሊየን አፍሪውያን በቫይረሱ ሊያዙ ይችላሉ ብለዋል።

ከዚህ ውስጥ 5 ነጥብ 5 ሚሊየን አፍሪካውያን የሆስፒታል እንክብካቤ እንደሚያስፈልጋቸውም በግሎባል ሄልዝ ይፋ ባደረጉት ጥናታቸው አስታውቀዋል።

ከ150 ሺህ እስከ 190 ሺህ አፍሪካውያን ደግሞ በቫይረሱ ሳቢያ ለህልፈት ሊዳረጉ ይችላሉም ነው ያሉት።

ይህ መሆኑ ደግሞ አሁን ላይ ወባን፣ ሳንባ ነቀርሳን እና ኤች አይ ቪ ኤድስን ለማከም ከሚደረገው ጥረት ጋር ተያይዞ አገልግሎት አሰጣጡን አስቸጋሪ ያደርገዋልም ነው ያለው።

የዓለም ጤና ድርጅት ቫይረሱ በአፍሪካ ሁለንተናዊ ቀውስ የማስከተል አቅሙ ከፍተኛ ስለመሆኑም ይገልጻል።

እስካሁን ባለው ሂደት ቫይረሱ በአፍሪካ የመስፋፋት አቅሙ ዝቅተኛ መሆኑንም ነው ድርጅቱ የገለጸው።

ይሁን እንጅ በደቡብ ሱዳን የስደተኞች መጠለያ ካምፕ ቫይረሱ ያለባቸው ስደተኞች መገኘታቸውን ተከትሎ፥ ቫይረሱ መዛመት የሚችልበትን እድል አግኝቷል ሲል ስጋቱን ገልጿል።

ምንጭ፦ ቢቢሲ

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.