Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያውያን አትሌቶች የሚጠበቁበት የሪጋ የዓለም የጎዳና ላይ ሩጫ ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 20፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያውያን አትሌቶች የሚጠበቁበት በላቲቪያ ሪጋ የሚሄደው የዓለም የጎዳና ላይ ሩጫ ውድድር ተካሂዷል፡፡

ኢትዮጵያ በሻምፒዮናው በሰባት ሴቶች እና በስድስት ወንዶች በድምሩ በ13 አትሌቶች ተወከላለች።

በሴቶች የ5 ኪሎ ሜትር ውድድር እጅጋየሁ ታዬ እና መዲና ኢሳ ከቀኑ 5፡50 ላይ ውድድራቸውን አድርገዋል፡፡ በዚሁ ርቀት 12፡15 ላይ በሚካሄደው የወንዶች ውድድር አትሌት ዮሚፍ ቀጄልቻ እና ሀጐስ ገ/ሕይወት ተሳትፈዋል፡፡

7፡00 ላይ በ1 ማይል ርቀት በሚከናወነው የሴቶች ውድድር አትሌት ድርቤ ወልተጂ እና ፍሬወይኒ ኃይሉ የተሳተፉ ሲሆን÷ በተመሳሳይ ርቀት 7:10 ላይ በሚካሄደው የወንዶች ውድድር አትሌት ታደሰ ለሚ ተሳትፏል፡፡

7፡30 ላይ በተደረገው የሴቶች የግማሽ ማራቶን ውድድር ደግሞ አትሌት ጽጌ ገ/ሰላማ፣ ያለምጌጥ ያረጋል እና ፍታው ዘርዬ ኢትዮጵያን ወክለው ተወዳድረዋል፡፡

በዚሁ ርቀት 8:15 ላይ በሚካሄደው የወንዶች ውድድር አትሌት ጀማል ይመር፣ ንብረት መላክ እና ፀጋዬ ኪዳኑ ተሳትፈዋል፡፡

ሁሉም ውድድሮች በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር ቀን ላይ እንደተካሄዱ የአትሌቲክስ ፌደሬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡

በዚህም ኢትዮጵያ በተለያዩ ርቀቶች ውድድር ድል ቀንቷት ውሏል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.