Fana: At a Speed of Life!

በሉዚያና በከባድ ጭጋግ ምክንያት ከ150 በላይ መኪናዎች እርስ በእርስ ተጋጩ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 13፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በአሜሪካ የደቡብ ሉዚያናን አውራ ጎዳናዎች ድቅድቅ ጭጋግ ሸፍኗቸው በርካታ የትራፊክ አደጋ መድረሱ ተነገረ፡፡

በጭጋጉ የአሽከርካሪዎች ዕይታ በመጋረዱ ከ150 በላይ ተሽከርካሪዎች እርስ በእርሳቸው እንደተላተሙ እና ቢያንስ የሰባት ሰዎች ሕይወት እንዳለፈ ሜትሮ አስነብቧል፡፡

የአደጋው ሰበብ ጠዋት ላይ አደጋው በደረሰበት አካባቢ ሰደድ እሳት ተነስቶ አካባቢው በድቅድቅ ጭስ በመሸፈኑ መሆኑ ተጠቁሟል፡፡

የሉዚያና ፖሊስ በአደጋው 158 የሚደርሱ ተሽከርካሪዎች እርስ በእርስ እንደተጋጩና 25 ሰዎች ላይ አደጋ እንደደረሰ ገልጿል፡፡

የሟቾች ቁጥር ሊያሻቅብ እንደሚችልም ያለውን ሥጋት አስቀምጧል፡፡

ከመኪኖች የእርስ በእርስ ግጭት በኋላ ከባድ እሳት እንደተነሳና አሽከርካሪዎችም ሁኔታውን ባለማመን ከመኪኖቻቸው ሲወጡ መታየታቸው ተነግሯል፡፡

የድረሱልን ጥሪ ሲያሰሙ የነበሩ ሰዎች መኖራቸውም ተመላክቷል፡፡

25 የሚሆኑት ላይ ከአነስተኛ እስከ አሳሳቢ ጉዳት ደርሶባቸው ወደ ሆስፒታል መወሰዳቸውም ነው የተነገረው፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.